"ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት ጦርነትን ሠርተዋል፤ የአሁኑ ትውልድ ደግሞ በውይይት ሀገርን መሥራት፣ መገንባት አለበት” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አካታች ሀገራዊ ምክክርን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ፣ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳዎችን መለየቱን እና የተሻለ ሥራም ሲያከናውን መቆየቱን ጠቁመዋል።
በቀጣይም በርካቶችን ባካተተ መልኩ አጀንዳዎቹ ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ሐሳቦችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል ብለዋል።
እስካሁን ባለው ሂደትም ኢትዮጵያዊያን የተቀራረበ ፍላጎት እንዳላቸው ትምህርት የሰጠ ስለመሆኑ ገልጸዋል።