Search

የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰበት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ ተበረከተለት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትስስር ፎረም የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰበት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ6 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁሶችና የተኝቶ ታካሚ አልጋን እንደሚያካትት የፎረሙ ሰብሳቢ እና የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አብደላ ከማል (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ድጋፉ ከአርባምንጭ፣ ከጂንካ እና ከዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ መደረጉን ገልፀው ወደፊትም ቀጣይነት እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ድጋፉ ዩኒቨርሲቲው ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንዲመለስ ከማገዙም በላይ፤ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ያለውን ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ሆስፒታሉን በተሻለ ቁመና ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ መሆኑን ነው ገልፀዋል።

በተመስገን ተስፋዬ

#ኢቢሲ #ኢቢሲዶትስትሪም #ወላይታሶዶዩኒቨርሲቲ #ድጋፍ