Search

ለመመካከር ፈቅዶ የመቀመጥ ጠቀሜታዎች

ሰኞ የካቲት 02, 2018 179

በዓለማችን ላይ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦች በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ እያለፉ ችግሮቻቸውንም በራሳቸው እየፈቱ አሁን ላለበት የስልጣኔ ደረጃ ደርሰዋል።
አብዛኛው አፍሪካዊ ማህበረሰብ ግጭቶችን የሚፈታበት መንገድ ተቀራራቢነት ቢኖረውም፤ ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው አንድ ቁልፍ ድርጊት አለ፤ እርሱም ለመነጋገር መቀመጥ ነው።
ለመመካከር መቀመጥ ለሀገራዊ ምክክር፣ ለግጭት አፈታት እና ለሌሎች የሰላም ግንባታ ሂደቶች ምን ዓይነት በጎ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ለሚለው የሚከተሉት ሀሳቦች ያብራራሉ፦
👉ሥነ-ልቦናዊ ጠቀሜታዎች፤
በግጭት ውስጥ ያሉ አካላት ለመነጋገር ፈቅደው ሲቀመጡ በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚገኙ በዚህ ዙሪያ የተካሄዱ ጥናቶች ያስረዳሉ።
ሰዎች ለመነጋገር ሲቀመጡ የመንፈስ መረጋጋት ውስጥ በመሆን፣ ራሳቸውን በመግዛት እና የማመዛዘን አቅማቸውን በመጠቀም የተረጋጋ ስብዕናቸው ዕውን ይሆናል፤ ይህም ለውይይት እና ለምክክር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
👉ዲሞክራሲያዊ ጠቀሜታዎች፤
ለመመካከር መቀመጥ ራሱን የቻለ የእኩልነት መገለጫ ነው። ሁሉም አካላት ለንግግር ሲቀመጡ አንዳቸው ከሌላቸው እንደማይበልጡ ማሳያ ነው።
ከዚህም ባሻገር ሀገራዊ ምክክርን በሚመስሉ መድረኮች ላይ ሰዎች ክብ ቅርፅ ሰርተው መቀመጣቸው የሀይል ሚዛንን ለማመጣጠን ይረዳል።
👉ማህበራዊ መተማመንን መሰረት ያደረጉ ጠቀሜታዎች፤
በሀገራዊ የምክክር ሂደት የሁሉም ባለድርሻ አካላት በአንድነት ለመነጋገር መቀመጥ እና መዘጋጀት እርስ በእርስ እንዲተማመኑ ያስችላቸዋል።
ይህም አንዱ ወገን ሌላኛው ወገን ያጠቃኛል ብሎ ከማሰብ ይልቅ፤ ተቃውሞውን፣ ስጋቱን እና ፍላጎቶቹን ለመናገርና የሌላውን ለማድመጥ እንዲፈቅድ በማድረግ መተማመንን ያጎለብታል።
*የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን