ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት፤ ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት አስጀምረናል ብለዋል።
ይህ አገልግሎት ዜጎች የፖሊስ አገልግሎትን በተሻለ ፍጥነት እና በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲያገኙ እንደሚያስችል ገልፀዋል።
በተጨማሪም አገልግሎቱ ለፖሊስ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለው እና የወንጀል መከላከል ስራውን የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የዚህ አገልግሎት መጀመር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የህግ አስከባሪ አካላት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተጀመረው የሪፎርም ስራን ውጤታማነት የሚያሳድግ ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው።
#EthiopianBroadcastingCorporation #Ebcdotstream #Ethiopia #SmartPoliceService #PMAbiy