Search

የግብርና ምርቶችን ወደ ውጭ ለሚልኩ አምራቾች ድጋፍ እናደርጋለን - ሲንቄ ባንክ

ሲንቄ ባንክ “በመትከል ማንሰራራት” የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በቡልቡላ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ አካሂዷል።

በመርሐ-ግብሩ የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት መኮንን ብሩ እንዲሁም የአዳማ እና የሻሸመኔ ዲስትሪክት ማናጅመንት አባላት እና ሠራተኞች ተሳትፈዋል።

ዛሬ የተተከሉት ለምግብነት የሚያገለግሉ ችግኞች መሆናቸውን የጠቀሱት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ ከዚህ ቀደም ተተክለው የነበሩ ችግኞች መፅደቃቸውንም ገልፀዋል።

ባንኩ ከሚሰጠው የፋይናንስ አገልግሎት በተጨማሪ ሀገራዊ ጥሪን ተቀብሎ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የቻለች ሀገር እንድትሆን አስቻይ ሁኔታዎች በመፍጠር ጥረት ባንኩ የሚሳተፍ መሆኑን ገልፀው፤ የግብርና ምርቶችን በማምረት ለውጭ ገበያ ለሚያቀርቡ አምራቾች ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

በብሩክታዊት አስራት

#EBC #EBCdotstream #SiinqeeBank #GreenLegacy