Search

ኢትዮጵያ በቂ አቅም ስለገነባች ባረጀ ውጫዊ ጫና ሸብረክ አትልም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ሰኔ 30, 2018 136

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በወቅታዊ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በውጭ ግንኙነት፣ በሀገራዊ አቅም ግንባታ እና በሉዓላዊነት ዙሪያ ትኩረቱን ባደረገው በዚህ ማብራሪያቸው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የገነባችው አቅም ከማንኛውም ያረጀ የጠላት ስልት በላይ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አሁን ያለው የዓለም ሁኔታ -ተገማች በሆነበት አውድ ውስጥ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አካሄድ 'ፕራግማቲክ' መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የሀገራችን የውጭ ግንኙነት መርሕ ነገር ሲደፈርስ እንዲጠራ መጠበቅ እና ሲጠራ መቅዳት መሆኑን በምሳሌ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚህም የኢትዮጵያን የውሳኔ ሰጪነት አቅም በማሳደግ የሌሎችን ጫና ላለመቀበል በትኩረት ተሠርቶ ውጤታማ መሆን መቻሉን አስታውቀዋል።

መንግሥት ከውጭ የሚደቀኑ ፈተናዎችን ለመመከት ሦስት ዋና ዋና "" መርሆዎችን ይዞ እየተጓዘ መሆኑንም አብራርተዋል።

እነዚህም ፈተናዎችን መቋቋም፣ ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር መጠቀም እንዲሁም ፈተናን መግራት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ዓለም በከፍተኛ ፈተና ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ የዚሁ ጥንካሬ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ሀገራዊ አቅምን የሚፈትኑ ጉዳዮችን በጥንቃቄ በመለየት እና ወደ ዕድል በመቀየር ጠንካራ አቅም መፈጠሩን አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ጠላት ይህንን ሀገራዊ እውነታ መካድ፣ መርሳት ወይም መጥፎ ምኞት ሊኖረው ቢችልም ኢትዮጵያ ግን ጠንካራ አቅም ስለገነባች ባረጀው የጠላት አካሄድ ፈጽሞ ሸብረክ እንደማትል በአጽንኦት ገልጸዋል።

ያረጀው የጠላትነት እና የመጠላለፍ ስልት ጊዜው ያለፈበት መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሁሉም አካላት ወደሚያዋጣው የሰላም እና ትብብር እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በለሚ ታደሰ