የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ በሁለቱ ሀገራት የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህል እና ሁለትዮሽ ግንኙነትን አጠናክረው በሚቀጥሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በቀጣናዊ፣ አኅጉራዊ እና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያሏትን ምልከታ ለሚኒስትሩ ገለፃ አድርገውላቸዋልም ነው ያሉት፡፡
የሩሲያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ እንዲሁም ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል ሩሲያ በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያም ሚኒስትሮቹ ውይይት አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡
በቶማስ ኃይሉ