Search

ጃፓን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂው የኒውክሌር ጥቃት ሲታወስ

ከ80 ዓመት በፊት አሜሪካ በጃፓን ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ ያደረሰችው የኒውክሌር ቦምብ ጥቃት አሰቃቂ መሆኑ በበርካቶች ዘንድ ይገለጻል።
 
በከተሞቹ የፈነዱት የኒውክሌር ቦንቦች ጎጂ አረር አሁንም ድረስ ሊወገድ ባለመቻሉ በሕፃናትና አዋቂዎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ስለመሆኑም ይነገራል።
 
ጃፓንም ጥቃቱ ያደረሰውን ጉዳት 80ኛ ዓመት በተለያዩ ሁነቶች አስባ ውላለች።
 
በዚሁ የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት ላይ የናጋሳኪ ከተማ ከንቲባ ሺሮ ሱዚኪ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በዚህ ሰዓት የዓለም ዋነኛው ስጋት ሆኗል ብለዋል።
 
 
 
ዓለም በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ከደረሰው አሰቃቂ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት ትምህርት ሊወስድ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
 
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሺገሩ ኢሺባ በበኩላቸው ሀገራቸው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ላለመያዝ እና ላለማምረት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም ጃፓን የኒውክሌር ጦርነት የሌለበት ዓለም እንዲሁም መሳሪያውም ጭምር የሌለበትን ስርዓትን ለመፍጠር ትሰራለች ብለዋል።
 
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጃፓን የአሜሪካንን እና የብሪታንያ የጦር መርከቦችን በመምታቷ አሜሪካ ወደ ጦርነቱ በመግባት ልክ በዛሬዋ ቀን እ.አ.አ. ነሐሴ 9 ፣ 1945 ናጋሳኪ ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ተጠቅማለች።
 
በከተማዋ የደረሰው ጥቃት ለ74 ሺህ ሰው ሕልፈት ምክንያት ሲሆን፤ የኒውክሌር ቦምቡ እስካሁን ድረስ ያደረሰው ጠባሳ የሚረሳ አይደለም።
 
ከናጋሳኪው ጥቃት ከሶስት ቀናት በኋላ ደግሞ ሌላኛው አሰቃቂ የኒውክሌር ጥቃት በሂሮሺማ ከተማ ላይ መፈጸሙን ታሪክ መዝግቦታል።
 
 
በሃብተሚካኤል ክፍሉ