Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታን አስጀመሩ

ሓሙስ የካቲት 12, 2018 120

ዛሬ የተጀመረው የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታ የበቆሎ እና የአኩሪ አተር ዱቄት እንዲሁም 14 ተጓዳኝ የበቆሎ ውጤት ምርቶችን ለማምረት የታቀደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን 2 ሺህ ቶን በቆሎ እና 120 ቶን አኩሪ አተር የማምረት አቅም ይኖረዋል።
ፕሮጀክቱ ከ6 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
አክለውም ለአካባቢው አርሶ አደሮች፣ ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ለግል ዘርፍ አምራቾች የእሴት ሰንሰለትን በማገዝ ለአካባቢው አርሶ አደሮች ሰፊ ገበያ ይፈጥራል፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ያሳድጋል ብለዋል።