"የኢትዮጵያ ሴቶች ከየት ወዴት" በሚል ሀሳብ በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀ መድረክ በሳይንስ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩ የሴቶች ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ተሳታፊነት በማጎልበት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እምቅ አቅምን ወደ ተገባር ለመቀየር የሚያስችል ምክክር የሚደረግበት ነው ተብሏል።
በመድረኩ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
በኢትዮጵያ 11 ሴት ሚኒስተሮች፣ 17 ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት ላይ ከ30 በላይ በዋና ዳይሬክተርነት እና በምክትል ዳይሬክተር እንዲሁም በተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች በርካታ ሴት አመራሮች አገራቸዉን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
በምንተስኖት ይልማ
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #MoWSA #Womenempowerment