Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ሴቶች የእውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው

እሑድ ነሐሴ 04, 2017 195

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት ሚና እንዲጎለብት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከኢትዮጵያ ሴቶች ልዩ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዕውቅናው የተሰጠው በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የሴት አመራሮች የምክክር መድረክ ላይ ነው።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመወከል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ሽልማቱን ተቀብለዋል።
የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሴት አመራሮችን በማብቃት እና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ "የኢትዮጵያ ሴቶች ያመሰግኑሃል" የሚል የምስጋና እና የእዉቅና ሽልማት አበርክተዋል።
በምንተስኖት ይልማ