Search

ከባድ ዝናብ ያስከተለው የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት እየፈተናት ያለችው ቻይና

በቻይና ጋንሱ ግዛት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 5 ተጨማሪ ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 22 ደርሷል።

የግዛቱ የጎርፍ ቁጥጥር እና የድርቅ እርዳታ ዋና መሥሪያ ቤት የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያመለክተው በጋንሱ ግዛት እስካሁን 15 ሰዎች ሲሞቱ 28 ሰዎች ጠፍተዋል።

ሌሎች 15 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን ወደ 10 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።

እንዲሁም በጓንግዶንግ ግዛት በዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት 7 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት በዋና ከተማዋ ቤጂንግ በጣለው ከባድ ዝናብ በከተማይቱ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ፣ የመሠረተ ልማት ውድመት እና የብዙ ሰዎችን መፈናቀል ተከትሎ በትንሹ 30 ሰዎች ሞተዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።

በቅርቡ በቻይና ምስራቃዊ፣ ሰሜናዊ እና ሰሜናዊ ምስራቅ የጣለው ከባድ ዝናብ ጎርፍ እና ሌሎች አደጋዎችን አስከትሎ በቤጂንግ፣ ሄቤይ፣ ጂሊን እና ሻንዶንግ ከተሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ዘገባው አትቷል።

በሴራን ታደሰ

#ebc #ebcdotstream #China #floods