Search

የጊደብ ወንዝ ድልድይን በአስቸኳይ ወደ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው

እሑድ ነሐሴ 04, 2017 185

የጊደብ ወንዝ ድልድይን በአስቸኳይ ወደ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ደብረማርቆስ ዲስትሪክት አስታውቋል።

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደቅረማርቆስ ጥገና ዲስትሪክት ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ አስረስ ለኢቲቪ እንደገለፁት መንገዱ ከፍተኛ የተሽከርካሪ ፍሠት ያለው በመሆኑ የመንገደኞች መስተጓጎል እንዳይፈጠር እየተሠራ ነው።

ችግሩ እንደተከሰተ በፍጥነት ጊዜአዊ ተገጣጣሚ የብረት ድልድይ እንዲገነባ የመንገዶች አስተዳደር ደብረማርቆስ ዲስትሪክት መረጃ እንደተሰጠው ቡድን መሪው ጠቀሰዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ተገጣጣሚ የብረት ድልድይ ከአዲስ አበባ እየተጫነ መሆኑን እና በቅርብ ጊዜ ለአገልግሎት እንደሚመቻችም ነው አቶ መንግስቱ የተናገሩት።

ከደብረማርቆስ ወደ ባህርዳር በሚወስደዉ መንገድ በጊደብ ወንዝ ላይ የተሰራዉ ድልድይ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ አደጋ የደረሰበት ሲሆን በደረሰው አደጋም አሁን ላይ የትራንሰፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን ተጠቁሟል፡፡

በራሄል ፍሬው