የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሶማሊኛ ቋንቋ ያዘጋጀው "ኡበድሰን" የልጆች መጽሔት በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት ተመርቋል።
መጽሔቱ ትውልድን በእውቀትና በመልካም ሥነ ምግባር ለመቅረጽ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በመጽሔቱ ምርቃት ላይ ተገኝተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የዲጂታል ሚዲያ በልጆች ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ መጽሔቱ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
መጽሔቱ የልጆችን የማንበብ ባህል በማሳደግ ነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር በትኩረት ይሠራል። ልጆች ስለ ሀገራቸውና ስለ ክልላቸው ታሪክ እንዲሁም ባህል በቂ እውቀት እንዲጨብጡ ያስችላቸዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መሳፍንት ተፈራ መጽሔቱ ልጆች በእውቀት ታንጸው እንዲያድጉ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
"ኡበድሰን" መጽሔት ማኅበራዊ ሚዲያ በልጆች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል። ይህ መጽሔት ድርጅቱ በሀገሪቱ በሦስት ቋንቋዎች ከሚያሳትማቸው የልጆች መጽሔቶች መካከል አንዱ ነው።
በቴዎድሮስ ታደሰ