የወደብ ጉዳይ ቀጣዩ የዓለም የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትኩረት መስክ ሆኗል ሲሉ የዓለም አቀፍ ገበያ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው በቀለ ተናገሩ፡፡
በቱርክሜኒስታን በተካሄደው የተመድ በማደግ ላይ ያሉ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ጉባኤ ላይ እየተነሱ የነበሩ ነጥቦች ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ እየተሰራበት መሆኑን ያሳየ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ገልፀዋል፡፡
ወደብ የሌላቸው ሀገራት በዓለም የማይታዩ እየሆኑ ነው ሲል የገለጸው ተመድ፤ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ምን ያህል እየሰራበት መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል አማካሪው፡፡
ኢትዮጵያም ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይዛ ወደብ አልባ ሆና መቀጠል እንደማትችልና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን እንዲረዳት እየሰራች ያለው ዲፕሎማሲዊ ግፊት ትክክለኛ ነው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለባህር በር የጂኦግራፊ ቅርበት ያላትና በታሪክም ከ30 ዓመታት በፊት የወደብ ባለቤት የነበረች ሀገር መሆኗን ያነሱት አቶ ጌታቸው፤ ላነሳችው ጥያቄ ከሁሉም ሀገራት ቀድማ ተቀባይነት ማግኘት አለበት ብለዋል፡፡
ወደብ አልባ ሆኖ መቆየት የንግድ ወጪን ያበዛል፣ መዋእለ ንዋይን ይቀንሳል እንዲሁም ዲጂታል ክፍታትን ይፈጥራል ሲሉም አቶ ጌታቸው በኢቢሲ የቅዳሜ መልክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
በመሀመድ ፊጣሞ
#ebcdotstream #seaaccess #ethiopia #LLDC3