Search

ሚኒስቴሩ በሶማሊ ክልል ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በሶማሊ ክልል ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዛሬ ጀምረዋል።

መርሐ-ግብሩን ያስጀመሩት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ፥ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ35 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለ10 አቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ ይከናወናል ብለዋል።

በሶማሊ ክልል፣ ለፈፈን ወረዳ ለ1 ሺህ 250 የአጋማ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደብተር፣ እስክሪብቶ እና እርሳስ እንዲሁም የደብተር ቦርሳን ጨምሮ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉም ተጠቅሷል።

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት እና የመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ ተሳታፊዎች ናቸው።

ተቋማቱ በሶማሊ ክልል ያስጀመሩት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 855 ሺህ ችግኞችን መትከልን ያካተተ ሲሆን፤ የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት 3 ሺህ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።

በላሉ ኢታላ

#ኢቢሲ #ኢቢሲዶትስትሪም #ሶማሊክልል #የበጎፈቃድአገልግሎት #አረንጓዴዐሻራ