በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና ፍጥነት በማከናወን የጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ከታቀደለት ጊዜ ፈጥኖ ዕውን እንዲሆን እንሠራለን ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
አቶ ኦርዲን በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙትን የአባድር ፕላዛ፣ የሐረር ላንድ ማርክ የኮሪደር ልማት፣ የመሶብ አንድ ማዕከል፣ የሐማሬሳና ኢኮፓርክ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ከተማዋን ለኑሮና ለሥራ ምቹ የማድረግ ቃልን በተግባር በመቀየር ረገድ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል።
በተለይ በሐረር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የከተማዋን ታሪካዊነት የሚያጎሉ፣ የቱሪዝም ማዕከልነቷን የሚያጠናክሩ እና የቱሪስት ፍሰቱንም የሚያሳድጉ ናቸው ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ ቅንጅታዊ አሠራርን ከማጎልበት ጀምሮ ሥራን ጀምሮ የማጠናቀቅ ተቋማዊ አቅም እንዲሁም የአመራር ቁርጠኝነት የታየበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#ኢቢሲ #ኢቢሲዶትስትሪም #ሐረሪክልል #የልማትፕሮጀክቶች