Search

"መጣ፣ ሔደ" የሚባል ሰው መሆን አልፈልግም - ኡስታዝ አቡበክር አህመድ

እሑድ ቤት ኡስታዝ አቡበክር አህመድን ዘይሯል።

በደሴ ከተማ ተወልደው ያደጉት ኡስታዝ አቡበክር፣ አባታቸው በሃይማኖታቸው ጠንካራ ስለነበሩ ከልጅነታቸው ጀምሮ ለእምነታቸው መሠረት እንደሆኗቸው ይናገራሉ።

በምድር ላይ መጥተህ መልካም ነገር መጨመር ካልቻልክ፣ አንተ ጭማሪ ሸክም ነህ የሚለውን አባባል አዘውተረው የሚጠቅሱት ኡስታዝ አቡበክር፤ "መጣ፣ ሔደ" የሚባል ሰው መሆን አልፈልግም፤ ለሀገሬ በጎ ነገር ጥዬ ማለፍ ነው የምፈልገው ሲሉ ይገልፃሉ።

በኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር እሴት እየተሸረሸረ በመምጣቱ ለምዕመናን የሚሰጡት ትምህርትም በአብዛኛው በዚሁ ርዕሰ-ጉዳይ ላይ እንደሚያጠነጥን እና ስለመከባበር፣ ስለመደጋገፍ፣ ስለፍትሐዊነት አብዝተው እንደሚሰብኩ ነው የሚናገሩት።

ሁሉም እምነት ለአማኙ ልክ ነው፤ አንዱ የሌላውን እምነት ማክበር እንጂ መናቅ እና ማንኳሰስ የለበትም፤ ሁሉም እምነቶች የሚያዙን ይህን እንድናደርግ ነው ብለዋል።

በቢታንያ ሲሳይ

#ኢቲቪ #ኢቢሲዶትስትሪም #እሑድቤት #ዚያራ #ኡስታዝአቡበክርአህመድ