Search

6.1 በሬክተር ስኬል የተመዘገበ ርዕደ-መሬት በቱርኪዬ ተከሰተ

በሬክተር ስኬል 6.1 የተመዘገበ ርዕደ-መሬት በምዕራባዊ ቱርኪዬ የተከሰተ ሲሆን፤ በተከናወነው የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማ መሠረት በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የቱርኪዬ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ምሽቱን በባሊከሲር ግዛት በተከሰተው ርዕደ-መሬት ሲንዲርጊ በሚባለው ቦታ አንድ ህንፃ መደርመሱን የቱርኪዬ የሀገር የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዬርሊካያ ተናግረዋል።

ርዕደ-መሬቱ የ11 ኪሎ ሜትር ገደማ ጥልቀት የነበረው መሆኑን የሀገሪቱ የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል።

በሴራን ታደሰ

#EBC #EBCdotstream #Türkiye #earthquake