Search

20ኛው የብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በልዩ ሁኔታ ይከበራል - አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል በልዩ ሁኔታ እንደሚከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።
አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የመሩት እና የክልል አፈጉባዔዎች የተገኙበት የበዓሉ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ውይይት ተካሂዷል።
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በ2018 ዓ.ም በሆሳዕና ከተማ በድምቀት እንደሚከበር ዐቢይ ኮሚቴው አስታውቋል።
አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የዘንድሮው በዓል በተለያዩ መመዘኛዎች ልዩ እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል።
ከፍ ባለ አቅም የሚከናወን በዓል መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ ዝግጅት ይከናወናል ሲሉ አንስተዋል።
ለዚህም በዓሉን በድምቀት ለማክበር በርካታ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል ሲሉ አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል።
የሕዝቦችን አንድነት በማጠናከር ፣ አብሮነትን እና ዴሞክራሲን በማጎልበት ረገድ በዓሉ ሚናው የላቀ መሆኑን አገኘሁ ተሻገር አስረድተዋል።
በዓሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መከበሩ ክልሉን ይበልጥ ለማስተዋወቅ እና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በወቅቱም የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል አከባበር መነሻ መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት የተደርጓል።
በአባዲ ወይናይ