Search

ሩሲያ በልዩ ሁኔታ የምታከብረው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የድል ቀን

ቅዳሜ ግንቦት 01, 2018 81

ሩሲያ የሁለተኛ ዓለም ጦርነት የድል ዕለትን በየዓመቱ ሜይ 9 በሞስኮ የሚገኘው ቀዩ አደባባይ በደማቅ ወታደራዊ ትርዒት ታከብራለች። ይህ የሩሲያ አከባበር በዓለም ላይ ካሉት ሀገራት ሁሉ እጅጉን የላቀ ድምቀት ያለው ነው። ይህ ታላቅ ትዕይንትሶቪየት ኅብረትበሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅትበናዚላይ ድል መቀዳጀቷን የሚያስታውስ እና ሩሲያውያን ልዩ የሀገር ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ነው። ሰልፉ ከድሉ መታሰቢያነቱ ባሻገርም እንደ ብሔራዊ የመታሰቢያ ቀን የሚታይ ሲሆን፣ ሩሲያ የጦር ኃይሏን አቅም እንዲሁም ታሪካዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ትኩረቷ መግለጫ ሆኖም ያገለግላል።

ናዚአውሮፓን በተቆጣጠረበት ወቅት እጅ ካልሰጡ ሀገራት መካከል ሩሲያውያን ይገኙበታል። የናዚ ጦር በመጀመሪያው ዙር ጦርነት ሶቭየት ሕብረትንጦር አሸንፎ የነበረ ቢሆንም ሩሲያውያን ግን እንደገና ተደራጅተው እስከ 27 ሚሊዮን ዜጎቻቸውን ሰውተው አሸንፈዋል። ይህ የሩሲያ መስዋዕትነት 15 እስከ 17 ከሚሆነው የአውሮፓ ሀገራት መስዋዕትነት የላቀ ሲሆን፣ በጦርነቱ ምክንያት በመላው ዓለም ከተከፈለው የሰው ህይወት 40 በመቶውን ገደማ እንደሚሸፍን የታሪክ ማስረጃዎች ያመላክታሉ።

የመጀመሪያው የድል ሰልፍ ሶቭየት ሕብረትየተካሄደውናዚከተሸነፈ ከአንድ ወር በኋላ .. ሰኔ 24 ቀን 1945 ነበር። በቀዩ አደባባይ በተካደው ሰልፍ ላይ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ስታሊን የተገኙ ሲሆን፣ ማርሻል ጆርጂ ጁኮፍ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጠው ሰልፉን መርተዋል።

በዚህ የመጀመሪያ ሰለፍ ላይ 40 ሺህ በላይ የሶቭየት ወታደሮች ተገኝተዋል። በዕለቱ በምርኮ ከተያዙ ወታደሮች የናዚ አርማዎችን የመጣል ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። ከሁሉም የሶቪየት ጦር ግንባር የተውጣጡ ወታደራዊ ክፍሎች እንዲሁም በጦርነቱ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችም ለእይታ ቀርበውበታል።

ምንም እንኳ የመጀመሪያው ሰልፍ የተካሄደው በፈረንጆቹ ሰኔ ወር ቢሆንም ናዚ ለመጨረሻ ጊዜ እጁን የሰጠው .. ሜይ 8, 1945 በበርሊን ነው። ሶቭየት ሕብረት ሜይ 9 የድል ቀን አድርጋ የምታከብረው በሰዓት አቆጣጠር ልዩነት (Time Zone) ምክንያት ነው።

በዓሉ በሶቭየት ሕብረት ውስጥ በተለዋወጡት ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ምክንያት በመሃል ቀዝቀዝ የማለት አዝማሚያ አሳይቶ ቆይቷል። .. 1965 እንደገና 20ኛው የድል በዓል ሲታወስ ግን የወቅቱ የሶቭየት ሕብረት ፕሬዚዳንት ሊዮኒድ ብሬዥኔቭ ሙሉ ወታደራዊ ሰልፍ በማድረግ ትውፊቱን እንደገና አነሱ። ይህም ሜይ 9 እንደገና የሕዝብ በዓል እንዲሆን የተደረገበት ክስተት ነበር።

1985 እና 1990 40ኛው እና 45ኛው ዓመት በግዙፍ ሰልፎች ተከብሯል። እነዚህ ክስተቶች ውስጣዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ዓለም አቀፋዊ ፀረ-ሾሳሊዝም በሰፈነበት ወቅት ሶቭየት ሕብረት የጦር አቅሟን ለዓለም ያሳየችበት ነበሩ።በሰልፎቹ የተደረጉት የድሉን ዐርበኞች በማክበር እና በቀዝቃዛው ጦርነት ምክንያት የተከሰተባትን ጫና መቋቋም እንደምትችል ወታደራዊ አቅሟን በማሳየት ላይ ነበር።

ከሶቭየት ሕብረት መፍረስ በኋላ ባሉት 1990ዎቹ መጀመሪያዎች ላይ ወታደራዊ ሰልፎች በሩሲያ አልተካሄዱም ነበር። ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ዕለቱ በድምቀት እንዲከበር ማድረግ ጀመሩ። 50ኛው ዓመቱ 1995 በፕሬዝዳንት ቦሪስ ዬልትሲን መከበሩ ግን ለበዓሉ መመለስ ወሳኝ ክስተት ነበር። 2000 መጀመሪያ እስከ አሁን በፕሬዚዳንት ፑቲን መሪነት በዓሉ በደማቅ ሰለፍ እየተከበረ ሲሆን፣ የሩሲያ ብሔራዊ ማንነት የማዕዘን ድንጋይ ተብሎ ይታሰባል።

ትዕይንቱ በሩሲያ ለድሉ አሸናፊዎች መታሰቢያ ከማድረግ ባለፈ የሀገሪቱን አቅም ማሳያ ሆኖ ያገለግላል። በሰልፎቹ የሩሲያን የኑክሌር ብቃት፣ እንደ T-14 Armata ያሉ ልዩ ታንኮች፣ የረቀቁ የጦር አውሮፕላኖች እና ጄቶች ይታዩበታል። ዜጎች "የማይሞት ሬጅመንት (Immortal Regiment)" የሚል ጽሑፍ ያረፈበት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዘመዶቻቸውን ፎቶግራፍ ይዘው ሰልፉ ላይ ይሳተፋሉ። ምዕራባውያን ሩሲያ ላይ ያላቸውን የተቃርኖ አስተሳሰብ እና ፋሺዝም የሚያወግዙ መልዕክቶች ይተላለፉበታል። ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት በሚያጋጥምበት ወቅት ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከርም ይጠቀሙበታል።

እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሰርቢያ ያሉ ሀገሮች በመሪዎቻቸው ወይም በተወካዮቻቸው አማካኝነት በበዓሉ ላይ ይሳተፋሉ።የምዕራቡ ዓለም ሩሲያ ዕለቱን በመጠቀም የጠበኝነት ፖሊሲ ታራምዳለች በማለት ይወቅሷታል።

የሩሲያ ማኅበረሰብም በዓሉን ብሔራዊ ኩራት አድርጎ ነው የሚወስደው። የሩሲያ ትምህርት ቤቶች ታሪክን በስፋት ያስተምራሉ። ቤተሰቦች የቀድሞ አባቶችን ጀግንነት የሚያሳዩ ሜዳልያዎችን፣ ፎቶዎችን እና ታሪኮችን ያሳያሉ። የጦርነት መዝሙሮች፣ ፊልሞች እና ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ከዚህ በዓል ጋር አብረው ይከበራሉ።

የዘንድሮው 81 ዓመት የሁለተኛ ዓለም ጦርነት መታሰቢያ እንደወትሮው በድምቀት እንደሚከበር ታውቋል። በዚህ በዓል ላይ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮቻቸው እንደሚገኙበት ታውቋል።

ቤላሩስ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ካዛኪዝታን፣ አርሜኒያ፣ ኪርጊስታን እና የሶቭየት ሕብረት የቀድሞ አባላት የሆኑ ሀገራት ዕለቱን ሜይ 9 ብሔራዊ በዓል እድርገው ያከብሩታል። ከምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ፈረንሳይ ዕለቱን ብሔራዊ በዓል አድርጋ የምታከብር ሲሆን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፖላንድ እና ሌሎች ሀገራት ዕለቱን አስበውት ይውላሉ። ደቡብ ኮሪያ ደግሞ ኦገስት 15 ዕለቱን አስባ ስትውል፣ ቻይና ደግሞ ሴፕቴምበር 2 ታስበዋለች።

አሜሪካ ሜይ 8 ዕለቱን አስባ የምትውል ቢሆንም በሀገሪቱ እንደ መደበኛ የፌዴራል ብሔራዊ የዕረፍት ቀን ተደርጎ አይከበርም።

በለሚ ታደሰ