Search

1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የፊታችን ረቡዕ ይከበራል

ሓሙስ ግንቦት 13, 2018 897

የ1447ኛው ዓ.ሒ (የ2018 ዓ.ል) የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል የፊታችን ረቡዕ እንደሚከበር የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ በዓሉን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ በመግለጫው፣ ዋናው የሐጅ ቀን (ውቅፍ ዓረፋ) ማክሰኞ ዙል ሒጃ 9 ቀን መሆኑን ጠቅሶ፣ ዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) ረቡዕ ዙል ሒጃ 10 (ግንቦት 19) ቀን ተከብሮ እንደሚውል አስታውቋል።

በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለጸው የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት፣ ምዕመናን በዓሉን ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመርዳት እንዲያከብሩት ጠይቋል።

#world #Ethiopia #Islam #Muslims #Eid #EidAlAdha #EBC

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: