በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጄኔቫ እየተካሄደ ባለው 79ኛው የዓለም የጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ በቅርቡ ይፋ በሆነው የህብረተሰብ ጤና ዳሰሳ ጥናት ግኝት መሠረት ኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት ሞትን በመቀነስ ረገድ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቧን ገልጸዋል።
በቀጣይም ለመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ጠንካራ የጤና ሥርዓት ለመፍጠር እና ዓለም አቀፍ የጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሠራ በአጽንኦት ተናግረዋል።
የጤና ባለሙያውን ተነሳሽነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በመላው ህብረተሰብ ተሳትፎና በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ የእናቶችና ህጸናት ጤናን በቀጣይነት ለማሻሻል እንዲሁም ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የጤና ልማት ግቦችን ለማሳካት ከዓለም የጤና ድርጅት፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከተለያዩ ሀገራት፣ ከሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
#Ethiopia #MoH #Geneva #WHA79 #EBC