Search

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዦን ካሴያ ጋር ተወያዩ

ማክሰኞ ሰኔ 02, 2018 39

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር / ዦን ካሴያ እና ከኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር / መቅደስ ዳባ ጋር ተወያይተዋል።

ከንቲባዋ በውይይታቸው በመጪው ኖቬምበር ወር ላይ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 5ኛውን ዓለም አቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ ለማካሄድ መመረጥዋንና ኮንፈረንሱን በጋራ ለማዘጋጀት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

አዲስ አበባ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመሰረተ ልማት በተሰሩ ስራዎች፣ በነዋሪዎቻችን እንግዳ ተቀባይነት፣ሰላሟ የተረጋገጠ ከተማ በመሆኗ እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ለማካሄድ ምቹ ከተማ መሆን በመቻሏ የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት እና ደህንነትን ማላቅ በሚል 5ኛውን ዓለም አቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ዝግጅቶች በስፋት በጋራ በመከናወን ላይ እንደሆነ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

5ኛውን ዓለምዓቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ የሃገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የህብረተሰብ ጤና መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎች፣ ተመራማሪዎች እና ባለድርሻ አካላትን የሚሳተፉበት ትልቅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ነው።