Search

ማንቸስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 2 ለ 1 አሸነፈ

እሑድ ነሐሴ 17, 2018 268

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስታዲየም ቦርንማውዝን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ቦርንማውዝ በ26ኛው ደቂቃ በታቨርኒየር ግብ መሪ መሆን ቢችሉም፣ ማንቸስተር ሲቲዎች በ85ኛው ደቂቃ በማርክ ጉሂ ግብ አቻ ሆነዋል።

 ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ በጭማሪ ሰዓት 90+2 ላይ ጆስኮ ግቫርዲዮል ሁለተኛዋን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሮ ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሏል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ብራይተን በአሜክስ ስታዲየም አስቶን ቪላን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: