Search

ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገር የጀግንነት ቅብብሎሽ አባትና ልጅ የሀገር ዘብ ሆነው ሲቆሙ

እሑድ ነሐሴ 17, 2018 71

ሀገር ማለት ሰው ነው፤ ሰው ማለት ደግሞ ሀገር። ሀገር ያለ ሰው፣ ሰውም ያለ ሀገር ባዶ ትርጉም ናቸውና ሁላችንም ሀገሬ ስንል እንቆረቆራለን፣ እንከፍላለን፣ እስከ ሕይወት ፍጻሜም መስዋዕት እንሆናለን።

የእኛ የኢትዮጵያውያን ሀገር ወዳድነት ደግሞ በቱባ የታሪክ ድርሳናት የተሞላ፣ የአብሮነትንና የጽናትን ክር ያስተሳሰረ ድንቅ ባህል ነው።

ከዚሁ ከአንዱ ማህፀን የተወለዱ ወንድምና እህቶች፣ አባቶችና ልጆች፣ ባልና ሚስቶች በተከበረው የሀገር መከላከያ ወታደራዊ አልባሳት ተጎናጽፈው ሀገራቸውን በክብር ያገለግላሉ፤ ስለ ሀገራቸው ሉዓላዊነትም ሕይወታቸውን ይሰጣሉ።

የብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ባስመረቀው 45 ዙር የኮማንዶና አየር ወለድ ሰልጣኞች የምረቃ በዓል ላይ የታየው የአባትና የልጅ ታሪክ ደግሞ፣ ይህ ታላቅ ሀገራዊ አደራ እንዴት በትውልድ ቅብብሎሽ እንደሚቀጥል ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አዲስ አሻራ ሆኗል።

ታሪኩ የሚጀምረው 1991 . ነው።ለሀገሬ ሰላም እዘምታለሁበሚል ጽኑ የሀገር ፍቅር ስሜት ወደ ሠራዊቱ የተቀላቀለው የአሁኑ ሌተናል ኮሎኔል ምትኩ ገብሩ፣ ላለፉት 27 ዓመታት ሀገሩን በታማኝነት፣ በጀግንነትና በጽናት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም በሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል ውስጥ ሆኖ በዚሁ የክብር መስመር ላይ ይገኛል።

ለሌተናል ኮሎኔል ምትኩ ውትድርና የሙያ ምርጫ ብቻ ሆኖ አልዘለቀም፤ ይልቁንም ለትውልድ የሚተላለፍ የክብርና የቃል ኪዳን ውርስ እንጂ።

በመሆኑም በጀግንነት የጀመረውን የወታደራዊ ጉዞ የሚያስቀጥል፣ ከአብራኩ የተከፈለው ልጅ ተክቶት የጀግኖቹን ሀገር እንዲጠብቅ በልቡ ሙሉነት ይመኝ ነበር።

የአባቱን የጀግንነት ገድልና የሀገር ፍቅር እየተመለከተ ያደገው ልጅ ምክትል አሥር አለቃ በረከት ምትኩ፣ ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ወታደር የመሆን ፍላጎት በልቡ ተለኩሶ ነበር።

እድሜው ባለመድረሱ ምክንያት በተደጋጋሚ ያደረጋቸው ሙከራዎች ባይሳኩለትም ተስፋ ሳይቆርጥ ሕልሙ እውን የሚሆንበትን ቀን በትዕግሥት ጠበቀ።

2014 . የአባቱን ፈለግ ተከትሎ ወደ ሠራዊቱ የተቀላቀለው በረከት፣ እጅግ ፈታኝ አካልንም አዕምሮንም የሚያደክመውን የኮማንዶ ስልጠና አልፎ ስኬት ላይ እንዲደርስ አባቱ ሌተናል ኮሎኔል ምትኩ ከጎኑ አልተለየም።

የሙያውን ክብር የሚያውቀው አባት ልጁን በምክርና በጠንካራ መንፈሳዊ ድጋፍ በማበረታታት 45 ዙር የኮማንዶ ምረቃ አብቅቶታል።

በምረቃው ዕለት ሌተናል ኮሎኔል ምትኩ በደስታና በኩራት ተሞልተውውትድርና የዱላ ቅብብል ነው፤ የእኔ ሀገርን የማገልገል ዘመን እንዳያቆም የአብራኬን ክፋይ ተክቼ የጀግኖችን ሀገር እንዲጠብቅ በማድረጌ እንደ አባት ታላቅ ኩራት ይሰማኛልሲሉ መናገራቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል።

ኮማንዶ በረከት ምትኩ በበኩሉ፣ በልጅነቱ ይመኘው የነበረው የአባቱ የጀግንነት ፈለግ ዛሬ ፍሬ አፍርቶ ቀዩን መለዮ በመልበሱ ታላቅ ደስታ እንደተሰማው ገልጾ፣ አባቶች ሀገርን ከነሙሉ ክብሯ አቆይተው ማለፋቸውንና የአሁኑ ትውልድም ይህን አርአያነት ተከትሎ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለሕዝቦቿ ደኅንነት በጽናት መቆም እንዳለበት ተናግሯል።

ትናንት በሀገራዊ ጀግንነት ሀገራቸውን ያቆዩት አባቶች የጣሉት መሠረት ዛሬም አልፈረሰም፤ እነ በረከት ምትኩም አደራውን ተረክበው ሀገርን በማጽናት ጉዞ ላይ የጀግንነት አሻራቸውን በማስፈር ላይ ይገኛሉ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: