Search

ከጥገኝነት ወደ ሉዓላዊነት፡ በተግባር እየተረጋገጠ ያለው የኢትዮጵያ የግብርና ስኬት

ሰኞ ነሐሴ 18, 2018 76

የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት እና ክብር የሚፀናው ሉዓላዊ በድንበርን በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ በምግብ ራስን በመቻል እና ጠንካራ የኢኮኖሚ ነፃነትን በማረጋገጥ ጭምር ነው።

ኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየውን የዕርዳታ ጥገኝነት ታሪክ በጥበብ እና በጠንካራ የሥራ ባህል በመቀየር፣ አሁን ላይ አስተማማኝ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችላት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (/) "በምግብ ራስን መቻል ዋነኛ ሀገራዊ አጀንዳችን ነው" ሲሉ ያስቀመጡትን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ፣ የተጀመረው የግብርና ልማት እና የምግብ ሉዓላዊነት ጉዞ ዛሬ በተግባር ፍሬ ማፍራት ጀምሯል።

በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተመዘገበው አስደናቂ ስኬት፣ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት ከመተካት አልፎ ምርትን ወደ ውጭ ገበያ መላክ የተጀመረበትን ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል።

ይህ የምግብ ሉዓላዊነት ጉዞ በስንዴ ልማት ብቻ የተገደበ አይደለም።

በበጋ እና በክረምት መስኖ ግብርና፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአቮካዶ እና በሌሎች የፍራፍሬ ልማቶች እንዲሁም ዘመናዊ ሜካናይዜሽንን በመጠቀም የምግብ ዋስትናን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለማረጋገጥ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ነው።

በተለይም 'የሌማት ትሩፋት' መርሐ ግብር የዜጎችን የአመጋገብ ሥርዓት በማሻሻል፣ ገበያን በማረጋጋት እና ለበርካታ ወጣቶች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ይህም ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን፣ ለም መሬቷን እና የውኃ ፀጋዎቿን አቀናጅታ በመጠቀም የራሷን ሕዝብ መመገብ የምትችል ትልቅ አቅም ያላት መሆኗን ለዓለም ያስመሰከረችበት ተግባራዊ ስኬት ነው።

የተጀመረው የግብርና ዘመናዊነት እና የምግብ ራስን መቻል ንቅናቄ የኢትዮጵያን ነገ በብርሃን እና በብልፅግና የሚያደምቅ፣ እንዲሁም የትውልዶችን ተስፋ የሚያለመልም ታሪካዊ እርምጃ ነው።

ኢትዮጵያ በፅናት እና በሥራ ወዳድነት የራሷን የምግብ ሉዓላዊነት እያረጋገጠች የታላቅነቷን ጉዞ በፅኑ መሰረት ላይ መገንባቷን ትቀጥላለች።

በሔዋን ጌታቸው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: