የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልሎች ተጠቃልለው የደረሱትን 24 የምርጫ ውጤቶችን ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ከየምርጫ ክልሎቹ ተጠቃልለው በመጡት ውጤቶች መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ 12 የክልል ምክር ቤት እና 11 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን አሸንፏል።
ፓርቲው በኦሮሚያ ክልል 8 የክልል ምክር ቤት እና 11 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች፣ በአማራ ክልል 2 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 1 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም በጋምቤላ ክልል 1 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ማሸነፉ ተገልጿል።
በሌላ በኩል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ክልል 1 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ማሸነፉን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚመራበት መመሪያ ተጠቃልለው የደረሱ የምርጫ ውጤቶችን ከሥር ከሥር ይፋ ለማድረግ የሚፈቅድለት በመሆኑ፣ በቀጣይም ተጠቃልለው የሚደርሱትን ተጨማሪ ውጤቶች በተመሳሳይ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
በሙሉ ግርማይ