Search

ኢትዮጵያ ለትውልድ የሚቀመጥ ዐሻራ እያኖረች ነው

ረቡዕ ሰኔ 10, 2018 59

ኢትዮጵያ ለቀጣይ ትውልዶች የምታስቀምጠውን አረንጓዴ ቅርስ ለማረጋገጥ በጽናት እየገሰገሰች ትገኛለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) 2018 . የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት፣ በዘንድሮው ዓመት ብቻ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ እንደተቀመጠ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በመርሐ ግብሩ እስካሁን ካከናወነችው ተግባር በመነሳት 65 ቢሊዮን ችግኞች የመትከልን ብሔራዊ ግብ ለማሳካት በጽናት እየተሰራ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል።

ይህ ንቅናቄ ከዛፍ ተከላ በዘለለ ትውልድን የማነጽ እና የአካባቢን ደኅንነት የማረጋገጥ ታላቅ ተልዕኮ አንግቧል።

የአየር ንብረት ለውጥ ዓለምን እየፈተነ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በጋራ የምትተክላቸው ችግኞች ነገ ለልጆቿ የምታስረክባቸው የንጹህ አየር፣ የለም መሬት እና የውኃ ደኅንነት ዋስትናዎች ናቸው።

የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻው ለወደፊት ትውልድ የሚቀመጥ ዘላቂ ሀብት በመሆኑ የዜጎችን አንድነት በማጠናከር፣ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የቀዳሚነት ሚና ይበልጥ እያጎለበተ ይገኛል።

ኢትዮጵያውያን በጋራ የጀመሩት ይህ ታላቅ ጉዞ፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ አስተማማኝ ቅርስ መሆኑም በግልጽ እየታየ ነው።

ኢትዮጵያ በየዓመቱ የምትተክላቸው በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች የሰላም፣ የልማት እና የብልጽግና ተስፋዎቿ መገለጫዎች በመሆናቸው ኢትዮጵያውን በአንድነት በመቆም ዐሻራቸውን ሊያሳርፉ ይገባል።

በሃና ምንዳሁን