Search

ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል

ሓሙስ ሰኔ 11, 2018 45

6ኛው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በዚህ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት ሒሳብ የፋይናንሺያል፣ የሕጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን እያዳመጠ ነው።

ሪፖርቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ እያቀረቡ ሲሆን፣ በሪፖርቱ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር የጥሬ ገንዘብ ጉድለት እየቀነሰ መምጣቱን እና ለዚህም የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መጠቀም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።

የገቢ ሒሳብን በሚመለከት 6.8 ቢሊዮን ብር ያልተሰበሰበ ቀረጥና ታክስ የገቢ ሒሳብ መኖሩን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

 ይህም በገቢ አሰባሰብ ላይ ያለውን ክፍተት እንደሚያሳይ ጠቁመው፤ በቀጣይ ተገቢው ክትትልና ጥረት መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።