የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ከተማ እና ክልል አቀፍ ፈተና (ሚኒስትሪ) በዛሬው ዕለት መሰጠት ጀምሯል።


ይህ ተማሪዎች ከመካከለኛ ደረጃ ወደ ቀጣዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት ወሳኝ ፈተና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ በኦሮሚያ፣ በሐረሪ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በሶማሊ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በጋምቤላ እና በሌሎችም ክልሎች መሰጠት ተጀምሯል።




ፈተናው ያለምንም እንከን በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓትም በየክልሎቹ በሚገኙ የተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።