Search

የኢትዮጵያን ክብር ከፍ ያደረገ ዲፕሎማሲ

ሓሙስ ሰኔ 11, 2018 37

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ታሪክ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረና ትልቅ መሠረት ያለው ቢሆንም፣ በየዘመናቱ በነበሩ የውስጥ አለመረጋጋቶች ሳቢያ የሀገረ መንግስት ግንባታው ሳይጠናቀቅ መቆየቱ በዲፕሎማሲያዊ ስኬቶቻችን ላይ የራሱን አሉታዊ ጥላ አሳርፎ መቆየቱ የታወቀ ሀቅ ነው።

በተለይም  ሀገራችን ለአስርት ዓመታት ተከታትሏት ከነበረው የጂኦስትራቴጂያዊ ኩስመና የቁልቁለት ጉዞ፣ ከጥርጣሬና ከስጋት መር አካሄድ ሙሉ በሙሉ በመላቀቅ፣ ዛሬ ላይ የራሷን ክብር በራሷ ውስጣዊ ጥንካሬና ያላሰለሰ ጥረት የምትመልስበት አዲስ ታሪክ በስፋት እየተጻፈ ይገኛል።

May be an image of the Oval Office

ይህ አዲስ ምዕራፍ ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን የታደሰ የአንከር ሀገርነት ቁመና የሚያጸና እና የዓለምን ኃያላን ትኩረት ወደ አዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ የሳበ ስር ነቀል ሽግግር ነው።

May be an image of text

ኢትዮጵያ የተከተለችው ሚዛናዊ፣ አጋርን ማብዛት ላይ ያተኮረ እና ፍፁማዊ ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ተራማጅ የውጭ ግንኙነት ፍልስፍና የዓለምን ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ ስቧል።

ሀገራችን በምዕተ ዓመቱ ያገኘችው ታላቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት እና የታሪክ አሻራ የBRICS ሙሉ አባል መሆን መቻሏ ነው። ይህ አባልነት በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ላይ ሰፊ የገበያና የኢንቨስትመንት አጋርነትን የሚፈጥር በመሆኑ፣ ለሀገራችን ብልፅግና መፋጠን የማይተካ ሚና ይጫወታል ።

No photo description available.

ይህ ስኬት የኢትዮጵያን ተሰሚነት ከፍ ከማድረጉም በላይ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ስትራቴጂካዊ ተወዳዳሪነት በሚገባ አረጋግጧል ። ከዚህ በተጨማሪም ሀገራችን በርካታ ዓለም አቀፋዊ ድሎችን በጽናት አስመዝግባለች፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባልና አፍሪካን በመወከል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና መመረጧ ፤ በዓለም የምግብ ፕሮግራም ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ውስጥ ለተጨማሪ ዓመታት እንድታገለግል መመረጧ፤ በአንድ በጀት ዓመት ውስጥ ብቻ ከ150 በላይ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ሁነቶችንና ኮንፈረንሶችን በአዲስ አበባ ማስተናገድ መቻሏ ፤ በአረንጓዴ አሻራ ዲፕሎማሲ ባስመዘገበችው ስኬት ሳቢያ ከ75 ሺህ  በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበትን ታላቁን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (COP32) ለማዘጋጀት የተሰጣት ዕድል ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አውራ መሆኗን ያረጋገጡ ትልልቅ ስኬቶች ናቸው ።

May be an image of text that says 'February February13,2026 13, 2026 AddisAbaba,Ethiopia Addis Ababa, Ethiopia Channel Channel5Português 5 Português SIE'

May be an image of one or more people, newsroom, dais and text

May be an image of text

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የግጭት መስክ ሳይሆን የትብብርና የጋራ ዕድገት አውድማ እንዲሆን የኃይል፣ የውሃ፣ የንግድ እና የመሰረተ ልማት ትስስሮችን ከጎረቤቶቿ ጋር በልዩ ትኩረት እየዘረጋች ትገኛለች ። የሱዳንን ቀውስ ለመፍታት እና በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን የተጫወተችው የመሪነትና የአሸማጋይነት ሚና በቀጠናው ያላትን የጸጥታ ዋስትና ያሳያል።

May be an image of text that says 'VARD ICA 8 > RICA WARD AFRICA FORWARD >> ICA VARD'

የቀይ ባህር በር ባለቤትነት እና ፍትሐዊ የባሕር በር ተጠቃሚነት ጥያቄዋን በሰላማዊ፣ በህጋዊ እና በሰጥቶ መቀበል መርህ በመምራት ከኩስመና ታሪክ ወደ ላቀ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ቁመና ለመሻገር አበክራ እየሰራች ነው። የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አቋሟም በውጭ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን መብት፣ ጥቅምና ሰብዓዊ ክብር ከማስጠበቅ ባለፈ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ግማሽ ሚሊዮን ዜጎችን በክብር ወደ ሀገራቸው እንድትመልስና ከሀገራት ጋር የሥራ ስምሪት ስምምነት እንድታደርግ አስችሏታል።

በአጠቃላይ፣ የትናንቱን የኩስመና ስብራት እና የቁልቁለት ጉዞ ሙሉ በሙሉ በመስበር፣ ሉዓላዊነትን እና ብሔራዊ ጥቅምን ከዜጎች ክብር እና ከሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ጋር ያቆራኘ አዲስና ንቁ ትውልድ በቆራጥነት ተነስቷል።

ስለሆነም፣ ይህ የዲፕሎማሲ ልዕልና እና የታደሰ ጂኦስትራቴጂካዊ ቁመና የሀገራችንን ገጽታ ከመለወጡም በላይ፣ ቀጣይነቱ የተረጋገጠ ብሔራዊ ክብርን ለሁላችንም አጎናጽፏል ። ኢትዮጵያ በቀጣይም በዓለም አቀፍ መድረክ ተፅዕኖ መፍጠር የምትችልና ድምጿ በእኩልነት የሚሰማላት አፍሪካዊት ኃይል ሆና መጓዟን በጽኑ ትቀጥላለች።