Search

የሀገራዊ ምክክር ማጠቃለያ ጉባኤ አመካካሪ ምሁራን የሥራ መመሪያና የክህሎት ሥልጠና መሰጠት ተጀመረ

ሓሙስ ሰኔ 11, 2018 37

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚያካሂደው ታላቁ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅት መጀመሩን አስታወቀ።

ጉባኤውን ለሚመሩ አመካካሪ ምሁራን የሚሰጥ የሥራ መመሪያና የሰባት ቀናት የክህሎት ሥልጠና በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

May be an image of one or more people, people studying and text

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ይህ የምክክር ሂደት በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግና ለሀገረ-መንግሥት ግንባታ እንዲሁም ለማኅበራዊ ስምምነት መሠረት የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሕዝባዊ አጀንዳዎችን በስፋት ሲያሰባስብ መቆየቱንና አሁን ላይ ሁሉንም ያካተተ የምክክር መድረክ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ ታሪካዊ ሥልጠና ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወከሉ ምሁራን የተሳተፉ ሲሆን፣ ከስዊድንና ከኔዘርላንድስ በመጡ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች አማካኝነት የክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።

May be an image of one or more people and text that says 'ONAL SSION, Cos 1 Hoile G GRAND A Addis. AddisAbaba Ababa'

May be an image of dais and text that says 'RIOPIAN o RIOPIANSUTIONAL RATIONAL 0 CONMISSION. YSM EVT C OODB Haile GRAND Addis AddisAbaba Ababa ዊ'

ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ምሁራኑ የተጣለባቸውን ይህንን ታሪካዊና ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ምክረ-ሀሳብ የሚያሰናዳበትን ታላቁን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በሐምሌ 8 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ለመጀመር የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ታውቋል።