Search

አረንጓዴ ዐሻራችን በተባበሩ ክንዶችና በመደመር የከበረ እሳቤ የመሥራት ምስክር ነው፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ሰኞ ሰኔ 15, 2018 77

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እንደ ሀገር የውበት ምንጭ እና የኢኮኖሚ ተደማሪ አቅም እንዲሆን ታቅዶ የተሠራ፣ አሁን ላይ በውጤት ፍሬ አፍርቶ እየታየ ያለ ተግባር መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር በመሆን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በጫካ ፕሮጀክት አካሂደዋል።

May be an image of tree

ይህ በተግባር የተደገፈ ግዙፍ የአረንጓዴ ልማት ጉዞ፣ ከኢኮኖሚያዊና የአካባቢ ጥበቃ ፋይዳው አልፎ በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ረገድ ለሀገራችን ትልቅ ክብር እና ተሰሚነት አጎናጽፏታል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት።

የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ በመሳብ ላይ የሚገኘው ይህ ስኬት፣ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን በኩራት ለማስተናገድ ለሚደረገው ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጠንካራና አስተማማኝ መሠረት የጣለ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ሁለንተናዊ እመርታ የመንግሥትንና የዜጎችን ትጋት የሚያሳይ እንዲሁም መላው ኢትዮጵያውያንን እጅግ ሊያኮራ የሚገባ ታላቅ ሀገራዊ ድል መሆኑን ጠቁመዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክታቸው፤ በዚህ ዓመት "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ያቀድነውን ግብ ለማሳካት ሁላችንም በኅብረት እንትከል፣ እንንከባከብ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: