Search

ከኡሁሩ ኬንያታ መልዕክት በስተጀርባ ያለው ሀገራዊ እውነት የኅብረ ብሔራዊነት ውበት እና የጋራ ድል

እሑድ ነሐሴ 17, 2018 89

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር፣ ኢትዮጵያ በኅብር ቀለም የተጋመደችና ታላቅነቷም መሠረት ይኸው ህብረ ብሔራዊነቷ መሆኑን በመጠቆም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ወገን ለብቻው ተነጥሎ ድል ማምጣት እንደማይችል አስገንዝበዋል።

ይህ ጥበብ የተሞላበት መልዕክት የሀገራችንን ነባራዊ እውነታና የነገ አቅጣጫ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ሲሆን፣ የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ባህሎችና እምነቶች ስብጥር የአንድነታችን ውበትና ሀገርን አጽንቶ የያዘ ዋና ዓምድ መሆኑን አብራርቷል።

ኢትዮጵያን በኅብር ቀለም ከተሸመነ ውብ ጨርቅ ጋር ማወዳደራቸው የልዩነቶችን አስፈላጊነት የሚያጎላ ሲሆን፣ በአንድ ጨርቅ ላይ ያሉ የተለያዩ ቀለማት ተቀላቅለው ማረፊያ ውበት እንደሚፈጥሩ ሁሉ፣ የኢትዮጵያም ብዝሃነት ተደምሮ ሀገራዊ ግርማ ሞገሷን የሚፈጥር ህያው ሀብት ነው።

በአሁኑ ወቅት የሚታየውንእኔ ብቻየሚል አስተሳሰብን የኮነኑት ኬንያታ፣ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ በኃይልም ሆነ በፖለቲካ የበላይነት አንዱ ወገን ሌላውን አግልሎ የሚጎናጸፈው ዘላቂ ድል አለመኖሩን አስምረውበታል።

በአንድ ሀገር ጥላ ሥር እየኖሩ የሌላውን ኅልውና መካድ የራስንም ኅልውና አደጋ ላይ መጣል በመሆኑ፣ ሀገራዊ አንድነትና ሰላም የሚረጋገጠው በኃይል የበላይነት ሳይሆን በውይይት፣ በፍትሕና በጋራ ተሳታፊነት ብቻ ነው።

የምክክር ጉባኤው መዝጊያ የመጨረሻው ግብ ሳይሆን የረጅም ጉዞ መጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን፣ ኢትዮጵያውያን የኅብረ ብሔራዊነታቸውን ውበት አምነውና የጋራ እጣ ፈንታ እንዳላቸው ተረድተው ሲንቀሳቀሱ ብቻ ታላቋን ኢትዮጵያ በከፍታዋ ላይ ማስቀጠል ይቻላል።

በአድማሱ አራጋው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: