የህዝብን ድምፅ በማክበር የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት እንደሚቀበል የጋምቤላ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለፀ
የምክር ቤቱ ሰብሳቢና በክልሉ የኢዜማ ምክትል መሪ ኮማንደር ጋትቤል ቦል ምርጫው ህዝቡ ይበጀኛል ያለውን በነፃነት የመረጠበትና የፖለቲካ ፓርቲዎችም ዓላማና አማራጮቻቸውን በስፋት ለህዝብ ያቀረቡበት ሂደቶች ውስጥ ያለፈ በመሆኑ የህዝብን ውሳኔ በማክበር ውጤቱን በፀጋ እንቀበላለን ብለዋል።
በምርጫው ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ መሳተፉ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልምምድ እየዳበረ መምጣቱን የሚያሳይ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
በአጠቃላይ የምርጫ ውጤት አሸናፊ ለሆነው ፓርቲና ለመራጩ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የደስታ መግለጫ መልዕክትም አስተላልፈዋል።
የህዝብ ድምፅ ትልቅ አደራ እና ሀላፊነት መሆኑን የጠቆሙት ኮማንደር ጋትቤል፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነቶችን በማጥበብ በአገራዊ ጉዳይ ላይ በመተባበር ከአሸናፊው ፓርቲ ጋር በመሆን የድርሻቸውን ሀላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም ገልፀዋል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: