የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው ታዋቂ የአውሮፕላን አምራች ዲ ሃቪላንድ (De Havilland) ኩባንያ ካዘዛቸው ዘመናዊ የዲ.ኤች.ሲ-6 ትዊን ኦተር ክላሲክ 300-ጂ (DHC-6 Twin Otter Classic 300-G) አውሮፕላኖች መካከል የመጀመሪያውን በይፋ መረከቡን አስታወቀ።

እነዚህ አዲስና ልዩ የሆኑ አውሮፕላኖች የአየር መንገዱን የውስጥና የቀጣናዊ በረራ አገልግሎት ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።
አውሮፕላኖቹ አስቸጋሪ በሆኑና ውስብስብ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጦች ውስጥ በቀላሉ የመብረርና የማረፍ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸው በመሆኑ፤ ለሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት፣ ለአየር ላይ ቅኝቶች፣ ለድንገተኛ የጤና አገልግሎቶችና ለሌሎች ተመሳሳይ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት የላቀ ጠቀሜታ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: