Search

አዲስ ከሚመሰረተው መንግሥት ጋር በጋራ በመሥራት ኢትዮጵያን ለማሻገር ዝግጁ ነን፡- የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች

ሰኞ ሰኔ 15, 2018 86

ግንቦት 24 ቀን የተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሆኖ በመጠናቀቁ መደሰታቸውን የገለጹት የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች፤ በዕለቱ የሚበጃቸውን አካል በመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በአግባቡ መተግበራቸውን አስታውሰዋል።

May be an image of one or more people

ይፋ በተደረገው የምርጫ ውጤት መሠረትም አዲስ ከሚመሠረተው መንግሥት ጋር በጋራ በመሥራት ኢትዮጵያን የማሻገር ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

አዲሱ መንግሥት የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት በትኩረት መሥራት እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።

በተለይም በተጀመሩ የልማት ስራዎች እና የኑሮ ማሻሻያዎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊሠራ እንደሚገባ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ መላው ኢትዮጵያውያንም በቀጣይ ከሚመሠረተው መንግሥት ጎን በመቆም ለሀገር ዕድገት ተግተው ሊሠሩ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በጀማል አህመድ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: