Search

አንጋፋው ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ሰኞ ሰኔ 15, 2018 240

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ሬዲዮ እና በቴሌቪዥን ለበርካታ ዓመታት ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አዘጋጅነት ያገለገለው ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ባደረበት ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ከአባቱ ታደሰ ዳምጠው እና ከእናቱ ፈለቀች ዳኜ ታህሳስ 26 ቀን 1959 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ።

ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ከታህሳስ 18/1994 ዓ.ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ቀን ድረስ ላለፉት 24 ዓመታት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተለይም በኢትዮጵያ ሬድዮ በተለያዩ ደረጃዎች አገልግሏል።

የጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ስርዓተ ቀብር ነገ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም በቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያ ከቀኑ 5፡30 ይፈጸማል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለሙያ ባልደረቦቹ መጽናናትን ይመኛል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: