የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገር ውስጥ መረጋጋትን እና ተዓማኒነትን መልሶ ማምጣቱን ገልጸዋል።
ይህም የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያውን ነፃ በማድረግ፣ የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲን በማዘመን፣ እንዲሁም ለዘላቂ እና አካታች ዕድገት ጠንካራ መሠረት ለመጣል የፋይናንስ ዘርፉን በማጠናከር የተገኘ መሆኑን “ኢትዮጵያ ታከናውናለች” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ አብራርተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: