አዲስ አበባ ዛሬ ላይ የያዘችው ማራኪ ገፅታ እና የኮሪደር ልማት ስኬት በቀላል ሳይሆን በአመራር ጥበብ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለውን አስቦ የመጨረስን ጥበብ በግልጽ ያሳየ ነው።
ብዙ ጊዜ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በሐሳብ ደረጃ ተጀምረው በተግባር የመንጠልጠል ወይም የመጓተት ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል።
በአዲስ አበባ የታየው የአመራር ቁርኝት ሐሳብን ከመውለድ ጀምሮ፣ በዝርዝር ዕቅድ መምራት፣ ቀን እና ሌሊት መከታተል እና ጥራቱን ጠብቆ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚቻል በተግባር ያረጋገጠ ነው።
ይህ ፈጣን እና ውጤታማ አፈፃፀም የአመራሩን የአስፈፃሚነት አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ክስተት ነው።
የዚህ ሌላው ትልቅ መገለጫ ውሳኔዎችን በጥናት እና በደፍረት የመተግበር ብቃት ነው።
የኮሪደር ልማት ሥራዎችን የሕዝብን የኑሮ እንቅስቃሴ ሳይገቱ እና ከተማዋን ሳያስተጓጉሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ከፍተኛ የአስተዳደር ጥበብን ይጠይቃል።
አመራሩ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ሐብትን በቁጠባ እና በውጤታማነት በመጠቀም እና የክትትል ሥርዓቱን በማጥበቅ ፕሮጀክቶችን በተባለው ጊዜ አስረክቧል።
ይህ ሂደት የአንድን አመራር ስኬት የሚለካው በተጀመሩ ሥራዎች ብዛት ሳይሆን ፍፃሜ ባገኙ እና ለሕዝብ አገልግሎት በበቁ ውጤቶች መሆኑን ያስመሰከረ ነው።
ከውበት ባሻገር በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ የሥነ-ልቦና ለውጥ ፈጥሯል።
ኅብረተሰቡ አስቦ መጀመር ብቻ ሳይሆን አስቦ መጨረስም ይቻላል የሚለውን እምነት እንዲያዳብር አድርጓል።
የአዲስ አበባ አዲሱ ገጽታ የውበት መገለጫ ብቻ ሳይሆን፣ ቁርጠኝነት፣ ዕቅድን የመፈፀም ደፍረት እና የአመራር ጥበብ የታየበት አዲሱ የልማት ተሞክሮ ነው።
በሃና ምንዳሁን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: