የተለያዩ የፌዴራል አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ያካተተው ተንቀሳቃሽ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአዲስ አበባ ሥራ ጀምሯል።
በመዲናዋ መስቀል አደባባይ ሥራ የጀመረው ይህ ተንቀሳቃሽ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በሌሎች ቦታዎችም እንደሚስፋፋ የፈዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል።
ከተጀመረ 1 ዓመት ያስቆጠረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ፈጣን አገልግሎት በማቅረብ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ መቻሉንም ገልጸዋል።
እስካሁን ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በማዕከሉ አማካኝነት አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልጸው፣ ይህንን የፌዴራል ተንቀሳቃሽ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በቀጣይ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ለማስፋት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በአባዲ ወይናይ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: