Search

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ ሆኖ ተወሰነ

ሰኞ ሰኔ 22, 2018 1099

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን ተወሰነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በ2018 የትምህርት ዘመን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ ከፍተኛ ዉጤት መመዝገቡን ጠቅሰው የተመዘገበው ውጤት አበራታች መሆኑን ተናግረዋል።

ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በ2018 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ በተማሪዎች ውጤት መረጋገጡን በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ ባደረገው ትኩረት ውጤቱ መመዝገቡን ተናግረው ፈተናውን በአጭር ጊዜ በማረም ውጤቱ ይፋ እንዲሆን ቀን ከሌት ሲሰሩ ለቆዩ የፈተና ክፍል ባለሙያዎችና ሂደቱን ሲደግፉ ለነበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በ2018 ዓ.ም 85,737 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: