Search

በመንግሥት ተቋማት የአገልግሎት ጥራትን እና የዜጎችን እርካታ ማሳደግ ተችሏል - የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ዓርብ ሰኔ 26, 2018 146

ባለፉት ወራት የመንግሥት አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች የአገልግሎት ጥራት እና እርካታ የሚገኝባቸው እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (/) ገለፁ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን 2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል።

በመድረኩ ላይ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (/) በበኩላቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

በተለይም የዲጂታላይዜሽን አሠራርን መተግበር ቀላል እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንዳስቻለ ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙት 102 የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎቶች 4 ሺህ 600 በላይ አገልግሎት በመስጠት የዜጎችን እርካታ እየጨመሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

መረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥን ለማጎልበት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የዜጎች መረጃ እንዲኖር ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ የሰው ኃይል መረጃ የማደራጀት ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝም ተነስቷል።

ሠራተኞችን ለማብቃት የሚሰጡ የብቃት ምዘናዎች ከሥራ መደቡ ጋር ግንኙነት ያላቸው እና የሥራ አፈፃፀምን የሚጨምሩ መሆናቸው በመድረኩ ተነስቷል።

በብሩክታዊት ተገኝ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: