Search

የጫኖ ጨንቻ መንገድ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የአካባቢውን የኢኮኖሚ ልማት ያፋጥናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዓርብ ሰኔ 26, 2018 147

የጫኖ ጨንቻ መንገድ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የማኅበረሰቡን ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክር፣ ንግድ እና ጉዞን እንዲሁም የአካባቢውን የኢኮኖሚ ልማት እንደሚያፋጥን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጫኖ ጨንቻ መንገድ ፕሮጀክት የደረሰበትን ፈጣን የግንባታ ሒደት በዛሬው ተመልክተዋል።

22 ኪሎ ሜትር የጫኖ ጨንቻ መንገድ እና 7 ኪሎ ሜትር የኤዞ-ጊርጫ ቅርንጫፍ መንገድን የያዘው 29 ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆኑን ገልጸው፣ 13.3 ኪሎ ሜትር ሥራው መጠናቀቁን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የመንገዱ ሥራ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የማኅበረሰቡን ትስስር ይበልጥ ያጠናክራል፣ ንግድ እና ጉዞን ያቀላጥፋል እንዲሁም የአካባቢውን የኢኮኖሚ ልማት ያፋጥናል ብለዋል።

በዚሁ ጉብኝታችን፣ 1997 . ጀምሮ በማኅበረሰቡ ጠንካራ መሪነት የያዘውና የታደሰውን የዶርዜ ሎጅ የቱሪዝም መዳረሻ ጎብኝተናልም ነው ያሉት።

40 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ፣ በቀዝቃዛውና ሰንሰለታማ የተራራ ጋራ ላይ ያረፈው ይህ አስደናቂ ሥፍራ፣ የአባያና ጫሞ ሐይቆችን እንዲሁምየእግዜር ድልድይተብሎ የሚጠራውን የተፈጥሮ ድንቅ ዕይታ በአንድ ላይ በግልጽ የሚያሳይ ውብ ገጽታን ይሰጣል ሲሉም አብራርተዋል።

እንደ ዶርዜ ሎጅ ያሉ መሰል የቱሪስት መዳረሻዎች ጎን ለጎን የሚከናወነው የመንገድ መሠረተ-ልማት መስፋፋት፣ ስፍራው ያለውን እጅግ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የባህል አቅም ሙሉ በሙሉ አውጥቶ ለመጠቀም በእጅጉ እንደሚያግዝም አመልክተዋል

 

በመሆኑም፣ በሀገር ውስጥ እና  በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የዲያስፖራ አባላት፣ እንዲሁም ከመላው ዓለም የሚመጡ ጎብኝዎች ይህንን አስደናቂ የተፈጥሮ ውበትና የበለጸገ የባህል ሐብት እንዲጎበኙና የታሪኩ ተጋሪ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: