1. ሌብነትን መከላከልና ታማኝነት፡- አንድ ትንሽ የሌብነት ድርጊት (ለምሳሌ የቱሪስት ሞባይል መስረቅ) የብዙ ዜጎችንና የሀገርን ስም ስለሚያጠፋ፣ ሌብነትና ቱሪዝም አብረው ስለማይሄዱ፣ ነዋሪው ቱሪስቶችን በመንከባከብ፣ ንብረታቸው ቢወድቅ እንኳ አንስቶ በመስጠት እና ታማኝ በመሆን የአካባቢውን መልካም ስም እንዲጠብቅ አደራ ብለዋል።
2. ሰላምን ማስቀጠል፡-አርባ ምንጭ እና አካባቢው በፍቅርና በሰላም የሚታወቅ በመሆኑ፣ ቱሪስቶች ያለምንም ስጋት በነፃነት (በማታም ጭምር) ተንቀሳቅሰው እንዲዝናኑ እና ገንዘብ እንዲያወጡ ይህን የሰላም እሴት ከምንም በላይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
3. ጽዳት እና አካባቢ ጥበቃ፡- ነዋሪው የራሱን ቤት ጠርጎ እንደሚያጸዳ ሁሉ ከተማውንም ከቆሻሻ በመጠበቅ እና ዛፎችን በመትከል አካባቢውን እንዲንከባከብ አሳስበዋል። ጽዳት እና ተፈጥሮን መጠበቅ፣ እንዲሁም ከተማን ባለቤት ሆኖ አለማቆሸሽ የአርባ ምንጭ ሰዎች መለያ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
4. የብሔር እኩልነት፣ አንድነት እና አብሮ መስራት፡- በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ብሔሮች (ኮንሶ፣ ጋሞ፣ ወላይታ፣ ዳሰነች፣ ጎፋ እና ሌሎችም) እኩል መሆናቸውን እና አንዱ ከአንዱ እንደማይበልጥ አበክረው ገልጸዋል።
"እኔ አንደኛ ነኝ" ወይም "እኔ እበልጣለሁ" ከሚል አግላይ ስሜት ወጥቶ፣ ፖለቲከኞች ለሚያመጡት አላስፈላጊ ሽኩቻ ጆሮ ሳይሰጡ፣ ለሀገር ልማትና ዕድገት በአንድነትና በመከባበር አብሮ መስራት እንደሚገባ በአጽንዖት ተናግረዋል። መሻል የሚለካው በተግባር እንጂ በስም አለመሆኑንም አስገንዝበዋል።