በ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ከሁለት ወራት በፊት የቀረበውን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ፣ ከተቋማትና ከክልሉ ባለሀብቶች ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ።
በዛሬው ዕለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የዚሁ ታላቅ ፕሮጀክት የምስጋናና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
ይህ ግዙፍ የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት፤ የታዋቂዎቹን የፍቅር ሐይቅ፣ የአሞራ ገደል እና የአሳ ገበያን ተፈጥሯዊ ጸጋቸውን በአግባቡ ጠብቀው እንዲለሙና ወደ ላቀ ዘመናዊነት እንዲሸጋገሩ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
ለልማት ፕሮጀክቱ አጠቃላይ ከሚያስፈልገው 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ ውስጥ 2 ቢሊዮን ብሩ በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ሲሆን፣ ቀሪው 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ደግሞ በሕዝብ ንቁ ተሳትፎና ድጋፍ የሚሸፈን መሆኑ ታውቋል።
በአሸናፊ እንዳለ