ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ አውድ እና የፖለቲካ ተዋናዮችን ሚና "የመጥረቢያ ፖለቲካ" በማለት በዘይቤ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው መጥረቢያን በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች በመክፈል የፖለቲካ አክተሮችን ተዋረድ አብራርተዋል።
እነዚህም ቆራጩ የብረት ክፍል፣ መያዣው እንጨት፣ እንዲሁም እንጨቱን ይዞ የሚቆርጠው ስውር አካል መሆናቸውን ዘርዝረዋል።
በማብራሪያቸውም የብረቱ ክፍል የራሱ የሆነ ዓላማ የሌለው እና የእንጨቱን ፍላጎት ብቻ ፈጻሚ መሆኑን ጠቅሰው፣ ህወሓትን ከዚህ ዓላማ አልባ ከሆነው የመጥረቢያው የብረት ክፍል ጋር አመሳስለውታል።
በሌላ በኩል ሻዕቢያን ለብረቱ እንደ መያዣ እንጨት ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን እና እንጨቱም በተራው ይዞ በሚያዘው እጅ ፍላጎት ብቻ እንደሚመራ አስረድተዋል።
ዋናዎቹ አዛዦች እና ባለጉዳዮች ከጀርባ ሆነው መጥረቢያውን የያዙት ሌላ አካላት መሆናቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ትግሉ ከብረቱ ወይም ከእንጨቱ ጋር ብቻ መሆን እንደሌለበት እና እንጨቱን የሚያዘው አካል እስካለ ድረስ ችግሩ በቀላሉ እንደማይፈታ አስገንዝበዋል።
በዮናስ በድሉ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: