Search

አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የሪቨር ፕሌት ስታዲየም በሆነው ኤል ሞኑመንታል የክብር አቀባበል ተደረገለት

ሰኞ ነሐሴ 18, 2018 51

በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር 56 ደቂቃ 51 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበው ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ከአስደናቂው ድሉ በኋላ ሌላ የማይረሳ አጋጣሚ አስተናግዷል።

የደቡብ አሜሪካው ኃያል ክለብ ሪቨር ፕሌት፣ ኢትዮጵያዊውን ጀግና በግዙፉ ስታዲየሙ ኤል ሞኑመንታል የክብር አቀባበል አድርጎለታል።

ዮሚፍ ስታዲየም በደረሰበት ወቅት በደጋፊዎችና በክለቡ አመራሮች ከፍተኛ የክብር አቀባበል ተደርጎለታል።

በሥነ ሥርዓቱም ላይ የሪቨር ፕሌት ክለብ ተወካዮች የዮሚፍን ስም እና ልዩ ስኬቱን የሚያጎላ የክለቡን ማሊያ በስጦታ አበርክተውለታል።

በአዲስ የሺዋስ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: