Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምስጋና አቀረቡ

ማክሰኞ ሰኔ 30, 2018 172

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የመንግሥትን ፖሊሲ በታማኝነት በማስፈጸም እና 30 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ እያከናወኗቸው ላሉ ስኬታማ ሥራዎች ምስጋና አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው እንዳብራሩት፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሕዝብን በማስተባበር ባሰባሰበው ሀብት በሁሉም ክልሎች የሞዴል እና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ከዚህም ባሻገር በግጭት ምክንያት የወደሙ፣ የተበላሹ እና የተቃጠሉ በርካታ ትምህርት ቤቶችን የመጠገን ሥራ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

እነዚህ የመልሶ ግንባታ እና የትምህርት ቤቶች ጥገና ሥራዎች በዋናነት የክልሎች ኃላፊነት ቢሆኑም፣ የትምህርት ሚኒስቴር እያሳየ ያለው ተነሣሽነት እና ጥረት ከፍተኛ ምስጋና የሚያሰጠው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መጽሐፍትን ከተለያዩ አካላት በማሰባሰብ እና ቴክኖሎጂን ወደ ትምህርት ሥርዓቱ በማስገባት በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን አንሥተዋል።

በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶች ካሉ ከመተቸት ይልቅ በመደገፍ፣ በማገዝ እና የጎደለውን በመሙላት የትምህርት ሚኒስቴርን የመሻሻል ጉዞ ማገዝ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በዮናስ በድሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: